የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ ማረጋገጥ አንዳሚገባ ትግልጽ።"
July 05, 2026 8 views
"የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ ማረጋገጥ ይገባል።"
‎ወ/ሎ ሁክሚያ መሀመድ
‎የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ሀላፊ
#DIREPROSPERITY | ሰኔ 26/2018
‎የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት የ2018 እቅድ አፈፃፀም፣ የ2019 እቅድ እንዲሁም የክረምት በጎ ፈቃድ ማቀጣጠያ መድረክ አካሄደ።
‎ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን ሴቶች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ ለማረጋገጥ በትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሎ ሁክሚያ መሀመድ ሲሉ መድረኩን በይፋ በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል።
‎የሴቶች ንፅህና መጠበቂያን በመደገፍ በትምህርት ቤት የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ሲገጥማቸው የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ በትምህርታቸው ውጤታማ ማድረግ ይገባል ያሉት ሀላፊዋ ወ/ሎ ሁክሚያ መሀመድ በቀጣይ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር የሚገኙ የኢኮኖሚ አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
‎በ2018 በጀት ዓመት በሴክተር፣ ወረዳና ክላስተር የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶችን በዋናነት የህብረትና የቤተሰብ አባላቶችን የማጥራት ሾል መሰራቱን የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሎ አይናለም መንገሻ በመድረክ ባቀረቡት የፅ/ቤታቸው ሪፖርት ጠቁመው አባላትን በአዲስ መልኩ የመመልመል ስራም በትኩረት መሰራቱን አክለው ገልፀዋል።
‎7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአስተዳደር ደረጃ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መልኩ በፓርቲያችን አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ የሴቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት የአንበሳውን ድርሻ መወጣት የቻሉበት ውጤታማ ሾል መሰራቱን ወ/ሎ አይናለም መንገሻ ተናግረዋል።
‎ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ ከሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ሾል መስራት ተችሏል።
‎ሴቶች በትምህርትና በጤና ማህበራዊ ዘርፍ አገልግሎቶች በተለይም በጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚ በማድረግ የሴቶችን ኑሮ ማሻሻል መቻሉም ተገልጿል።
‎በመድረኩ ላይ የአስተዳደሩ ሴክተር ተቋማት፣ የከተማ ወረዳና የገጠር ክላስተሮች የ2018 እቅድ አፈፃፀም በዝርዝር አቅርበዋል።
‎የአባላት ገቢ አሰባሰብ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፣ አምስት ሚሊየን ኮደርስ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ ምሁራንን መሰረት ያደረገ አዳዲስ ወጣት ሴት አባላቶችን መመልመል እና ሌሎች መሰል ስራዎች በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራት ናቸው።
‎በመጨረሻም የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅድ የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም በመድረክ በቀረበው የ2018 አፈፃፀምና የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እቅድ ላይ ሀሳብና አስተያየት ሰጥተው ከመድረክ አወያየዮች ተገቢው ምላሽ ተሰጥቶበት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

 

Share: